Main Menu
Interview with Kibirt Zenebework Aregaw
Aend-Ethiopia Interview with Kibirt Zenebework Aregaw on Her 80th Birthday Anniversary 08-28-2010, Washington, DC. Click Here to LISTEN

Sheraton Addis (251)(11) 517171

Sheraton Addis (251)(11) 517171
EthioGreen LLC is a registered import / export company located in Washington, DC
202-558-8337
EthioGreen
President Obama Explains Healthcare

President Obama Explains Healthcare.gov
Ethiopian Political Parties
Ethiopian Political Parties
ESFNA ETHIOPIAN DAY July 2, 2010
ESFNA ETHIOPIAN DAY July 2, 2010

Ethiopian Television ETV Satellite Frequency
Aend-Ethiopia YouTube

አማርኛ ዜና

በዩጋንዳው ፍንዳታ የተጠረጠሩት አራት ኢትዮጵያዊያን በነጻ ተለቀቁ

ፍንዳታውን አድርሰዋል የተባሉት አጥፍቶ ጠፊዎች ምስል

በዩጋንዳው ፍንዳታ የተጠረጠሩት አራት ኢትዮጵያዊያን በነጻ ተለቀቁ

የዩጋንዳ ፖሊስ ፍንዳታውን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ ጥቃቶቹ በሁለት አጥፍቶ ጠፊዎች መከናወናቸውን አስታውቆ፤ በጥርጣሬ የተያዙት ኢትዮጵያዊያን መለቀቃቸውን አረጋግጧል።

የፖሊሱ አዛዥ ካሌ ካይ-ሁራ ለጋዜጠኞች ሲናገሩ በፍንዳታው ከተሰበሰቡት አስከሬኖች መካከል የሁለቱን ሬሳ ፈልጎ የመጣ ሰው አልተገኘም። የሁለቱን ሰዎች ማንነት የሚያሳዩ ምስሎችንም ፖሊስ አሳይቷል።

በአለም አቀፍ የወንጀለኛ አዳኝ ፓሊስ ኢንተር-ፖል ድረ ገጽ የሚገኙት እንደገና የተሰሩ ምስሎች የአጥፍቶ ጠፊዎቹን ማንነት ከሞላ ጎደል እንደሚያሳዩም ተጠቁሟል። አንደኛው ሰው ሶማሊያን ጨምሮ ከአፍሪካ ቀንድ ሰዎች የፊት ምስል ጋር የሚቀራረብ የቆዳ ቀለም ያለው ሰው ሲሆን፤ ሌላኛው ሰፋ ያለ ፊትና ጥቁር የቆዳ ቀለም ያለው ነው።

የፖሊሱ አዛዥ ካሌ ካይሁራ እነዚህ ሰዎች የአጥፍቶ ጠፊዎች መሆናቸውን በእርግጠኝነት ይናገራሉ።

“እነዚሁ ሁለት አስከሬኖች፤ ከሌሎቹ ሬሳዎች በተለየ መልኩ፤ መጥቶ ስጡን ያለ ሰው የለም። አሁን አንድ ሳምንት ሆኗል። ሁሉም አስከሬኖች በዘመድ ተለይተው ርክክብ ተደርጓል። እነዚህን የጠየቀ የለም፤ ይሄ ደግሞ አጋጣሚ ሊሆን አይችልም፣” ብለዋል።

ካይሁራ አክለውም የሰዎቹን ማንነት ለማወቅ አለም አቀፍ ዘመቻ መጀመሩን አስታውቀዋል።

“ኢንተር-ፖል፤ FBI እና ሌሎች አጋር የፖሊስ ሀይሎች ስራዮ ብለው ፍለጋውን ቀጥለዋል። ማንነታቸውን ማወቅ ለምርመራችን ወሳኝ ስለሆነ፤ በአለም ዙሪያ የነዚህን ሰዎች ማንነት እያስፈለግን ነው።”

ለዚህ ምርመራ የተለያዩ የፖሊስ ግብረ-ሀይሎች ወደ ካምፓላ አምርተዋል። የአሜሪካው የደህንነት ተቛም FBI ከ60 በላይ መርማሪዎቹን ልኳል። የዩጋንዳው እለታዊ ሞኒተር ጋዜጣም የኢትዮጵያ የደህንነት ሰራተኞችም ምክር እየሰጡ መሆናቸውን አስነብቧል።

የኢትዮጵያ ደህነንት ባለስልጣናት የካምፓላውን ፍንዳታ ያቀነባበረው ግለሰብ አሁንም አለመያዙን መጠቆሙን ዴይሊ ሞኒተር ጽፏል። የሰውየውን ማንነት ያልጠቀሱ መንጮችን የጠቀሰው ዘገባ ተጠርጣሪው የሶማሊያ ዜጋ መሆኑን አስነብቧል።

የዩጋንዳ ፖሊስ ከፍንዳታዎቹ ጋር በተያያዘ 20 ሰዎችን አስሯል። እነዚህም  ዩጋንዳዊ፣ ፓኪስታናዊ፣ ኢትዮጵያዊና ሶማሊያዊ ዜግነት ያላቸው መሆናቸው ተጠቁሟል።

የፖሊስ አዛዥ ካሌ ካይሁራ ከነዚህ ሰዎች መካከል ተጠርጥረው የተያዙት ኢትዮጵያዊያን መፈታታቸውን ተናግረው፤ በፍንዳታው የውጭ ሀይሎች እጅ እንዳለበት ገልጸዋል።

“ከዚህ ፍንዳታ ጋር በቀጥታ የተገናኙ ሰዎችን መለየት የሚቻልበት ጊዜ ላይ አይደለግም። ገና ብዙ ስራ ይጠብቀናል በፍጥነት የምንናገረው የለም። መረጋገጥ ያለባቸው መረጃዎች አሉን። በነገራችን ላይ ፓኪስታናዊያን ብቻ አይደሉም፤ ከመካከላቸው ዩጋንዳዊያንም አሉበት።”

ለዚህ ፍንዳታ ሀላፊነቱን በሶማሊያ የሚንቀሳቀሰው የእስልምና አክራሪ ቡድን አል-ሸባብ ሀላፊነቱን ወስዷል። አልሸባብ “ፍንዳታዎቹ የአፍሪካ ህብረት የሰላም አስከባሪዎች የሚገድሏቸው ሰዎችን ደም ይበቀላል” ማለቱ ይታወሳል።

ማለዳ ተፈተዋል የተባሉት ኢትዮጵያዊያን እስከ ሰኞ ማታ ድረስ በእስር መዋላቸውን በካምፓላ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን አረጋግጠዋል።

Aend Ethiopia June 14, 2010

Read more

Here is the Music Player. You need to installl flash player to show this cool thing!

Aend-Ethiopia Radio Address (Ethiopian 4th General Election 2010)

የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ የአራተኛውን ጠቅላላ አገር አቀፍ ምርጫ የመጨረሻ ውጤት ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14 2002 (ሬዲዮ ፋና) የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ግንቦት 15 ቀን የተካሄደውን አራተኛ ዙር ጠቅላላ አገር አቀፍ ምርጫ የመጨረሻ ውጤት ዛሬ ይፋ አደረገ ።የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ካሉት 547 መቀመጫዎች መካከል የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር(ኢህአዴግ) 499 መቀመጫዎችን አግኝቷል ። ዛሬ ቦርዱ የምርጫውን የመጨረሻ ውጤት ይፋ ባደረገበት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የቦርዱ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መርጋ በቃና እንዳሉት በመራጭነት ከተመዘገበው ከ31 ሚሊዮን ከሚበልጠው ህዝብ መካከል 29 ነጥብ 8 ሚሊዮኑ ማለትም 93.4 በመቶው ድምፁን ሰጥተቷል።

በውጤቱም 547 መቀመጫ ካለው የህዝብ ተወከካዮች ምክር ቤት መካከል የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) 499 መቀመጫዎችን ማግኘቱን ፕሮፌሰር መርጋ በቃና ተናግረዋል ። በሶማሌ ክልል የሶማሌ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /ሶህዴፓ/ 24 መቀመጫ ፣ የቤኒሻንጉል ጉምዝ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ / ቤጉህዴፓ/ 9 ፣ የአፋር ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /አብዴፓ/ 8 ፣ የጋምቤላ ህዝቦች አንድነት ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ / ጋህአዴን/ 3 ፣ የሀረሪ ብሄራዊ ሊግ / ሀብሊ/ 1 ፣ የአርጎባ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት /አህዴድ/ እና የኢትዮጵያ ፌዴራሊያዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ( መድረክ) አንድ አንድ መቀመጫዎችን ሲያገኙ አንድ የግል ተወዳዳሪም አሸንፈዋል ።ይህ ውጤት በትክክል የህዝብ ፍርድ መሆኑን አረጋግጣለሁ ብለዋል ፕሮፌሰር መርጋ ።

እንደ ፕሮፌሰር መርጋ ጉዳያቸውን ወደ ፈርድ ቤት ይዘው የሄዱ ፓርቲዎችም ካሉ ጉዳየ ከዚህ በኋላ ፍርድ ቤትን የሚመለከት ይሆናል ።ቦርዱም ፍርድ ቤት የሚሰጠውን ማንኛውንም ውሳኔ ለመቀበል ዝግጁ መሆኑንም አስታውቀዋል ። ቦርዱ ሰኔ 11 ቀን 2002 ባካሄደው አስችኳይ ስብሰባ ግንቦት 15 በመላው አገሪቱ የተካሄደው ጠቅላላ ምርጫ ውጤት ከየምርጫ ክልል ተጠቃሎ መግባቱን አረጋግጧል ። ህጉን ተከትሎ ለቦርዱ ቀርቦ ውሳኔ ያላገኘ አቤቱታ አለመኖሩንም ተመልክቷል ።

በመሆኑም ውጤቱን በጥልቀት መርምሮ በማፅደቅ ለህዝብ ይፋ አንዲሆን መወሰኑን የቦርዱ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መርጋ በቃና ተናግረዋል ። ይህ ውጤት በትክክል የህዝብ ፍርድ መሆኑን አረጋግጣለሁ ብለዋል ፕሮፌሰር መርጋ ። ቀደም ሲል ቦረዱ ያወጣውን ጊዜያዊ የምርጫ ውጤት መሰረት አደርገው የቀረቡ አቤቱታዎች እንደነበሩ ያነሱት ፕሮፌሰር መርጋ በቃና ፥ የቀረቡት አቤቱታዎች በማስረጃ ያልተደገፉ ናቸው ነው ያሉት ።

ቦርዱ የአራተኛውን አገር አቀፍ ምርጫ የመጨረሻ አጠቃላይ ውጤቱን ይፋ ከማድረጉ በፊት ምላሽ ያላገኘ ምንም ዓይነት አቤቱታ አለመኖሩን እንዳረጋገጠ ፕሮፌሰር መርጋ በቃና ውጤቱን ይፋ ባደረጉበት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተናግረዋል ። ቦርዱ በቅንነት የተመለከታቸው እነዚህ አቤቱታዎች ያለማስረጃ የቀረቡ በመሆናቸው ምንም ማድረግ አይችልም ብለዋል ።

<<<<<<<=>>>>>>>

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14 2002 (ሬዲዮ ፋና) የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ግንቦት 15 ቀን የተካሄደውን አራተኛ ዙር ጠቅላላ አገር አቀፍ ምርጫ የመጨረሻ ውጤት ዛሬ ይፋ አደረገ ።የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ካሉት 547 መቀመጫዎች መካከል የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር(ኢህአዴግ) 499 መቀመጫዎችን አግኝቷል ። ዛሬ ቦርዱ የምርጫውን የመጨረሻ ውጤት ይፋ ባደረገበት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የቦርዱ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መርጋ በቃና እንዳሉት በመራጭነት ከተመዘገበው ከ31 ሚሊዮን ከሚበልጠው ህዝብ መካከል 29 ነጥብ 8 ሚሊዮኑ ማለትም 93.4 በመቶው ድምፁን ሰጥተቷል።

ቦርዱ የአራተኛውን አገር አቀፍ ምርጫ የመጨረሻ አጠቃላይ ውጤቱን ይፋ ከማድረጉ በፊት ምላሽ ያላገኘ ምንም ዓይነት አቤቱታ አለመኖሩን እንዳረጋገጠ ፕሮፌሰር መርጋ በቃና ውጤቱን ይፋ ባደረጉበት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተናግረዋል ። ቦርዱ ሰኔ 11 ቀን 2002 ባካሄደው አስችኳይ ስብሰባ ግንቦት 15 በመላው አገሪቱ የተካሄደው ጠቅላላ ምርጫ ውጤት ከየምርጫ ክልል ተጠቃሎ መግባቱን አረጋግጠጧል ። ህጉን ተከትሎ ለቦርዱ ቀርቦ ውሳኔ ያላገኘ አቤቱታ አለመኖሩንም ተመልክቷል ። በመሆኑም ውጤቱን በጥልቀት መርምሮ በማፅደቅ ለህዝብ ይፋ አንዲሆን መወሰኑን የቦርዱ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መርጋ በቃና ተናግረዋል ። ዛሬ ቦርዱ የምርጫውን የመጨረሻ ውጤት ይፋ ባደረገበት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ፕሮፌሰር መርጋ እንዳሉት በመራጭነት ከተመዘገበው ከ31 ሚሊዮን ከሚበልጠው ህዝብ መካከል 29 ነጥብ 8 ሚሊዮኑ ማለትም 93.4 በመቶው ድምፁን ሰጥተቷል ።

በውጤቱም 547 መቀመጫ ካለው የህዝብ ተወከካዮች ምክር ቤት መካከል የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) 499 መቀመጫዎችን ማግኘቱን ፕሮፌሰር መርጋ በቃና ተናግረዋል ። በሶማሌ ክልል የሶማሌ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /ሶህዴፓ/ 24 መቀመጫ ፣ የቤኒሻንጉል ጉምዝ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ / ቤጉህዴፓ/ 9 ፣ የአፋር ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /አብዴፓ/ 8 ፣ የጋምቤላ ህዝቦች አንድነት ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ / ጋህአዴን/ 3 ፣ የሀረሪ ብሄራዊ ሊግ / ሀብሊ/ 1 ፣ የአርጎባ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት /አህዴድ/ እና የኢትዮጵያ ፌዴራሊያዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ( መድረክ) አንድ አንድ መቀመጫዎችን ሲያገኙ አንድ የግል ተወዳዳሪም አሸንፈዋል ። በክልል ምክር ቤቶች ደግሞ 152 መቀመጫ ባለው በትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ( ህወሓት/ ኢህአዴግ) 152 መቀመጫዎችን ፣ 96 መቀመጫ ካለው በአፋር ክልል የአፋር ብሄራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ/አብዴፓ/ 93 መቀመጫ እንዲሁም የአርጎባ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት/አህዴድ/ 3 መቀመጫዎችን አግኝተዋል ።

294 መቀመጫ ባለው በአማራ ብሄራዊ ክልል ምክር ቤት የብሄረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ብአዴን/ኢህአዴግ) ሁሉንም መቀመጫዎች አሸንፏል ። በኦሮሚያ የክልሉ ምክር ቤት ካለው 537 መቀመጫዎች ውስጥ የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ /ኢህአዴግ) ሙሉ በሙሉ አግኝቷል ። 186 መቀመጫ ባለው በሶማሌ ክልል ምክር ቤት ደግሞ የሶማሌ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ሶህዴፓ) ሁሉንም መቀመጫዎች ይዟል ። 99 መቀመጫ ካለው የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ምክር ቤት 98 መቀመጫዎች የቤኒሻንጉል ጉምዝ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /ቤጉህዴፓ/ ሲያገኝ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት(መኢአድ) አንድ መቀመጫ አግኝቷል ።

የደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ካለው 348 መቀመጫዎች መካከል ሁሉንም የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ(ደኢህዴን/ኢህአዴግ ) ሁሉንም መቀመጫ ያገኘ ሲሆን ፥ የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት ካለው 156 መቀመጫዎች መካከል የጋምቤላ ህዝቦች አንድነት ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ጋህአዴን/ ሙሉ በሙሉ አግኝቷል ። በሀረሪ ክልል ደግሞ የክልሉ ምክር ቤት ካለው 36 መቀመጫ ውስጥ የሀረሪ ብሄራዊ ሊግ /ሀብሊ/ 18 መቀመጫ የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ /ኢህ አዴግ) 18 መቀመጫዎችን አግኝተዋል ። ይህ ውጤት በትክክል የህዝብ ፍርድ መሆኑን አረጋግጣለሁ ብለዋል ፕሮፌሰር መርጋ ።

ቀደም ሲል ቦረዱ ያወጣውን ጊዜያዊ የምርጫ ውጤት መሰረት አደርገው የቀረቡ አቤቱታዎች እንደነበሩ ያነሱት ፕሮፌሰር መርጋ በቃና ፥ የቀረቡት አቤቱታዎች በማስረጃ ያልተደገፉ ናቸው ነው ያሉት ። ቦርዱ በቅንነት የተመለከታቸው እነዚህ አቤቱታዎች ያለማስረጃ የቀረቡ በመሆናቸው ምንም ማድረግ አይችልም ብለዋል ። እንደ ፕሮፌሰር መርጋ ንግግር ጉዳያቸውን ወደ ፈርድ ቤት ይዘው የሄዱ ፓርቲዎችም ካሉ ጉዳየ ከዚህ በኋላ ፍርድ ቤትን የሚመለከት ይሆናል ። ቦርዱም ፍርድ ቤት የሚሰጠውን ማንኛውንም ውሳኔ ለመቀበል ዝግጁ መሆኑንም አስታውቀዋል ።

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ የተባበሩት መንግስታት ለሚያሰገነባው ህንጻ የመሰረት ድንጋይ አኖሩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14 2002 (ሬዲዮ ፋና) ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ የተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን በሰባት ነጥብ አምስት ሚሊዮን ዶላር አዲስ አበባ ውስጥ ለሚያስገነባው ሕንጻ የመሰረት ድንጋይ አኖሩ፡፡ የኮሚሸኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አብዱላሂ ጃኒን በስነስርዓቱ ላይ እንደገለጹት በካዛንቺስ አካባቢ የኢትዮጵያ መንግስት ለድርጅቱ በሰጠው ስፍራ ላይ የሚገነባው አዲስ ህንጻ ሁለት ዓመት በማይሞላ ጊዜ ውሰጥ የሚጠናቀቅ ነው፡፡

ህንጻው በተባበሩት መንግስታት ስር ለሚሰሩ የተለያዩ ድርጅቶች የሚያገለግል ሲሆን አሁን ያለውን የቢሮ ጥበትም እንደሚያቃልል አመልክተዋል፡፡ ራማ በተባለ አገር በቀል የኮንስትራክሽን ተቋራጭ ድርጅት አማካኝነትየሚገነባው ይኽው ህንጻ በ23 ወራት ውስጥ ስራው እንደሚጠናቀቅም ታውቋል፡፡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅ በአፍሪካ ውስጥ ወደፊት በሚያካሂዳቸው ስብዓዊ አገልግሎቶችና የልማት ስራዎች በርካታ የስው ኃይል እንደሚያስፈልጉት ጠቁመው በቀጣዮቹ አመታት ለሚቀጠራቸው ለነዚህ ሰራተኞች ተጨማሪ ቢሮዎች መስራት አስፈላጊ መሆኑን አብራረተዋል፡፡

ይህንን ፍላጎት ለማሟላት የኢትዮጵያ መንግስት በተለይም የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ከድርጅቱ ቅጥር ግቢ ጋር ተያያዥነት ያላውን 29 ሺህ ሜትር ስኩየር ስፍራ ለሕንጻው ግንባታ መፍቀዱ መዲናዋ የዓለምአቀፍ ዲፕሎማሲ መናሃሪያነቷን ይበልጥ ያጎላዋል ብለዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የሕንጻውን የመሰረት ድንጋይ ለማኖር በስፍራው መገኘታቸው ለጉዳዩ መንግስታቸው የሰጠውን ትኩረትና ቁርጠኝነት ያሳያል ሲሉ ገልጸዋል፡፡ አዲሱ ህንጻ በአብዛኛው በአገር ውሰጥ በሚመረቱ ቁሳቁሱች እንደሚገነባ ለማወቅ ተችሏል፡፡

ህንጻው ዘመናዊ የእሳት አደጋና ሙቀተን የሚቆጣጠር የደህነነት መሳሪያዎችም ይኖረዋል፡፡ ለቢሮ ሕንጻው የሚገጠሙ የሙቀትና የቅዝቃዜ መቆጣጠሪያ መሳሪያዎችም አካባቢን የማይጎዱና በጸሐይ ሐይል የሚሰሩ መሆኑም ታውቋል፡፡ በስነስርአቱ ላይ ተቀማጭነታቸው አዲስ አበባ ውሰጥ የሆኑ የተለያዩ አገራት አምባሳደርች ተገኝተዋል፡፡ የተባበሩት መንግስታት የኢኮኖሚ ኮሚሽን መቀመጫውን አዲስ አበባ ውስጥ ሲያደርግ 50 ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ በነዚህ አመታት ውሰጥ ኮሚሽኑ የራሱን ጽህፈት ቤት ከመስራቱ ባሻገር የአፍሪካ መስብሰቢያ አዳራሽ፣ የተባበሩት መንግስታት የስብሰባ ማዕከል ማስገንባት ችሏል፡፡

Leave a Reply

Making a donation to Aend-Ethiopia radio station
ON AIR WUST 1120 AM Sunday 3PM - 4PM
Thank you for your donation.
Aend-Ethiopia Service Payment
Service Payment
Aend-Ethiopia Radio Address (Ethiopian 4th General Election 2010)

Aend-Ethiopia Interview with Honorable Prof Beyene Petros

Here is the Music Player. You need to installl flash player to show this cool thing!

Aend-Ethiopia Interview with Eng. Hailu Shawel

Here is the Music Player. You need to installl flash player to show this cool thing!

Aend-Ethiopia MP3 Player JW

Here is the Music Player. You need to installl flash player to show this cool thing!

TORONTO CANADA
PM MELES ZENAWI IN TORONTO CANADA
Main Menu
September 2010
S M T W T F S
« Aug    
 1234
567891011
12131415161718
19202122232425
2627282930  

Videos, Slideshows and Podcasts by Cincopa Wordpress Plugin